የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በግንቦትና በሰኔ ወር የጉባኤ ሽማግሌዎች ትምህርት ቤት በክልላችን እየተሰጠ ነበር። ትምህርት ቤቱ፣ ወንጌላዊና ቀናተኛ አስተማሪ በመሆን የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ስላገኘነው መብት ጎላ አድርገው የሚገልጹ ክፍሎች ነበሩት። የአምላክን ፈቃድ ማድረግ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ማስተማርና ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተመልሶ ለመጠየቅ የታሰበበት ጥረት ማድረግን ይጨምራል። እስካሁን በተካሄዱት ስምንት ትምህርት ቤቶች ወደ 320 ገደማ የሚሆኑ ሽማግሌዎች የተካፈሉ ሲሆን ይህም በአገራችን ካሉ ሽማግሌዎች መካከል ግማሽ የሚያህሉት በትምህርት ቤቱ ሠልጥነዋል ማለት ነው። እነዚህ ወንድሞች ባገኙት ትምህርት በጣም የተደሰቱ ሲሆን ሥልጠናው በጉባኤያቸው በሚያከናውኑት አገልግሎት ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጥርጥር የለውም።