ታኅሣሥ 31 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
w09 11/15 ከገጽ 7 አን. 1 እስከ ገጽ 8 አን. 8 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሚልክያስ 1-4 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ “በመጠበቂያ ግንብ ላይ የሚወጣ አዲስ ዓምድ።” በንግግር የሚቀርብ። በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀው የአቀራረብ ናሙና የሚገኝበትን የመንግሥት አገልግሎታችን እትም በመጠቀም በጥር ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ሉቃስ 10:38-42 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ በጥርና በየካቲት የምናበረክተው ጽሑፍ። በውይይት የሚቀርብ። በጥርና በየካቲት ከሚበረከተው ጽሑፍ ውስጥ ትኩረት የሚስቡ የተወሰኑ ነጥቦችን ከተናገርክ በኋላ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 55 እና ጸሎት