ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ታኅሣሥ፦ ከሚከተሉት ትራክቶች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል! ወይም እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? ግለሰቡ ፍላጎት ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አሊያም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ በተባለው ብሮሹር ተጠቅማችሁ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንደሚችል ልታሳዩት ትችላላችሁ። ጥር እና የካቲት፦ ከሚከተሉት ባለ32 ገጽ ብሮሹሮች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት ወይም የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። መጋቢት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ በ2014 የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ሰኞ፣ ሚያዝያ 14 ይሆናል።
◼ በመጋቢት 2013 ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ አስፋፊዎች በዚያ ወር እንደምርጫቸው 30 ወይም 50 ሰዓት ማገልገል ይችላሉ። በተጨማሪም የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን የሚጎበኘው በመጋቢት ወር ከሆነ በዚያ ወር ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ አስፋፊዎች በሙሉ (ለማገልገል የመረጡት 30ም ሆነ 50 ሰዓት) የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ከዘወትር አቅኚዎች ጋር በሚያደርገው ስብሰባ ላይ እስከ መጨረሻው መገኘት ይችላሉ።
◼ የሚከተሉት አዳዲስ ጽሑፎች ስለደረሱን ማዘዝ ትችላላችሁ፦ ሶማልኛ፦ ሪል ፌዝ—ዩር ኪ ቱ ኤ ሃፒ ላይፍ፣ ትራክት ቁ. 27 (መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል!)፣ ትራክት ቁ. 72 (ዘ ግሬተስት ኔም)