ጥር 14 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥር 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 52 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
w09 11/15 ከገጽ 10 አን. 18 እስከ ገጽ 11 አን. 24 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማቴዎስ 7-11 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ማቴዎስ 10:24-42 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አስተዋይ በመሆን ከንቱ ነገሮችን ከመከተል ተቆጠቡ—1 ሳሙ. 12:21፤ ምሳሌ 23:4, 5 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ልንጸልይባቸው የሚገቡ ትክክለኛ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?—rs ገጽ 294 አን. 1-8 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ እርዳታ መስጠት። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 188 አንቀጽ 4 እስከ ገጽ 189 አንቀጽ 4 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ሌሎች አሳቢነት ስላሳዩት እድገት ማድረግ ለቻለ አንድ አስፋፊ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ማቴዎስ 4:1-11 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ‘የተሟላ ምሥክርነት ስጡ።’ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 47 እና ጸሎት