የካቲት 18 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 18 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መዝሙር 52 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 1 ከአን. 16-20 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 1-4 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ማርቆስ 2:18 እስከ 3:6 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የመንጽሔ ትምህርት የተመሠረተው በምን ላይ ነው?—rs ገጽ 298 አን. 2 እስከ ገጽ 299 አን. 3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ጳውሎስ በ1 ቆሮንቶስ 7:29-31 የሰጠውን ምክር መረዳት የሚኖርብን እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ በአስቸጋሪ ወቅት ቃሉን ስበኩ። (2 ጢሞ. 4:2) በ2012 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 72 ከአንቀጽ 1-2፣ ገጽ 110፣ ከገጽ 156 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 157 አንቀጽ 1 እንዲሁም ገጽ 179 አንቀጽ 3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
15 ደቂቃ፦ “የመታሰቢያውን በዓል የምናስተዋውቅበት ዘመቻ መጋቢት 1 ይጀምራል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት አንድ ቅጂ ለሁሉም አድማጮች እንዲታደል አድርግ፤ ከዚያም ይዘቱን በአጭሩ ከልስ። አንቀጽ 2 ላይ ስትወያዩ የጉባኤውን ክልል ለመሸፈን ስለተደረገው ዝግጅት እንዲናገር የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹን ጋብዝ። አንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ ደግሞ የቀረበውን የመግቢያ ሐሳብ በመጠቀም መጋበዣ ወረቀቱ ሲበረከት የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 8 እና ጸሎት