የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የ2012 የአገልግሎት ዓመት 9,502 የሚያህል ከፍተኛ አዲስ የአስፋፊዎች ቁጥር እና 2.4 በመቶ ጭማሪ አግኝተን ተደምድሟል። በዚህ የአገልግሎት ዓመት 531 አዳዲስ ደቀ መዛሙርት ተጠምቀዋል። በድምሩ 703,015 መጽሔቶች የተበረከቱ ሲሆን ይህ ደግሞ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ቁጥር ነው። በአማካይ 7,203 ጥናቶች ተመርተዋል፤ እንዲሁም በርካታ ሰዎች ፍላጎት አሳይተዋል። በተጨማሪም 14 ሰዎች ማንበብና መጻፍ የተማሩ መሆኑን ስንገልጽላችሁ ደስ ይለናል። መምህራኑም ሆኑ ተማሪዎቹ ላደረጉት ጥረት ሊመሰገኑ ይገባል።