መጋቢት 11 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 38 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 2 ከአን. 15-20 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 13-16 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ማርቆስ 14:22-42 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የመታሰቢያው በዓል ትርጉም ምንድን ነው?—rs ገጽ 265 አን. 3 እስከ ገጽ 266 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚቀርቡት ምሳሌያዊ ቂጣና ወይን ምን ያመለክታሉ?—rs ገጽ 266 አን. 3-4 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ማቴዎስ 10:7-10 እና ሉቃስ 10:1-4 እንዲነበቡ አድርግ። ከዚያም እነዚህ ዘገባዎች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅሙን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።
10 ደቂቃ፦ አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች—ክፍል 1። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 111 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 112 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አገልግሎታቸውን ለማስፋት ሲሉ ወደ ሌላ አካባቢ ለተዘዋወሩ ወይም ሌላ ቋንቋ ለተማሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። የትኞቹን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መወጣት ችለዋል? ቤተሰባቸው ወይም ጉባኤው የረዳቸው እንዴት ነው? ምን በረከት አግኝተዋል?
10 ደቂቃ፦ “የመታሰቢያውን በዓል ለማክበር በደስተኛ ልብ ዝግጅት አድርጉ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ጉባኤው ለመታሰቢያው በዓል ያደረጋቸውን ዝግጅቶች ተናገር። የመጋበዣ ወረቀቱ ሥርጭት ያለበትን ደረጃ ተናገር።
መዝሙር 8 እና ጸሎት