መጋቢት 18 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 3 ከአን. 1-9 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 1-3 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሉቃስ 1:24-45 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በጌታ ራት ላይ ከሚቀርበው ምሳሌያዊ ቂጣና ወይን መካፈል የሚገባቸው እነማን ናቸው?—rs ገጽ 267 አን. 2-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የመታሰቢያው በዓል መከበር የሚኖርበት በየስንት ጊዜው ነው? የሚከበረውስ መቼ ነው?—rs ገጽ 268 አን. 2-3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
12 ደቂቃ፦ “ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ሁለት ክፍሎች ያሉት ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጀመሪያው ክፍል አንድ አስፋፊ ቅድሚያውን ወስዶ በዓሉ ላይ ለተገኘ አንድ እንግዳ ጥሩ አቀባበል ሲያደርግ የሚያሳይ ነው። ሁለተኛው ደግሞ አስፋፊው፣ የግለሰቡን ፍላጎት ይበልጥ ለማነሳሳት እንዲያስችለው ከፕሮግራሙ በኋላ ከእሱ ጋር በዘዴ ቀጠሮ ለመያዝ ጥረት ሲያደርግ የሚያሳይ ነው።
18 ደቂቃ፦ “በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው? የተባለውን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት መንገድ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ ከጥናቱ ጋር በአንድ ትምህርት ላይ ሲወያይ የሚያሳይ የሰባት ደቂቃ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 20 እና ጸሎት