የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/13 ገጽ 3-4
  • ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 3/13 ገጽ 3-4

ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፦

በሰማይ የሚኖረው አባታችን ይሖዋ፣ ፍቅር በማሳየት ረገድ ተወዳዳሪ የሌለው ምሳሌ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ “አምላክ ፍቅር ነው” በማለት ይናገራል። (1 ዮሐ. 4:8) ይሖዋ ሁሉን ቻይ ቢሆንም “አምላክ ኃይል ነው” የሚል አገላለጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ አናገኝም። የይሖዋ አገዛዝ በዋነኝነት የተመሠረተው በፍቅር ላይ ነው። ይህ በእርግጥም ወደ እሱ ለመቅረብ የሚያነሳሳን ትልቅ ምክንያት ነው!

ደስ የሚለው፣ ይሖዋ እንድናገለግለው አያስገድደንም። እሱ ፈላጭ ቆራጭ ገዥ አይደለም። ለእሱ ባለን ልባዊ ፍቅር ተነሳስተን እንድናገለግለው ይፈልጋል። እንዲህ ስናደርግ አገዛዙ ትክክል እና ፍቅር የሚንጸባረቅበት በመሆኑ ገዢያችን እንዲሆን ፍላጎት እንዳለን እናሳያለን። የሰው ዘር ታሪክ የሚያሳየውም ይህንኑ ነው።

ይሖዋ አዳምና ሔዋን እንዲታዘዙት ከማስገደድ ይልቅ የራሳቸውን ምርጫ እንዲያደርጉ አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል። አዳምና ሔዋን ይሖዋን ከልብ ቢወድዱት እንዲሁም ላደረገላቸው ነገሮች አድናቆት ቢኖራቸው ኖሮ ሰይጣን በይሖዋ ላይ እንዲያምፁ ያቀረበላቸውን ፈተና ማሸነፍ ይችሉ ነበር።

ከጊዜ በኋላ ሙሴ ለእስራኤል ብሔር የመጨረሻ ንግግሩን ባቀረበበት ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦ “እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፣ ሞትንና ጥፋትን በፊትህ አኑሬአለሁ።” (ዘዳ. 30:15) እስራኤላውያን ሕይወታቸውን ስለሚመሩበት መንገድ የራሳቸውን ምርጫ የማድረግ ነፃነት ነበራቸው። ኢያሱም እስራኤላውያንን “እግዚአብሔርን ማምለክ የማያስፈልግ መስሎ ከታያችሁ . . . የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ” ብሏቸው ነበር። ሕዝቡም “እግዚአብሔርን መተው ከእኛ ይራቅ” በማለት መልሰዋል። (ኢያሱ 24:15, 16) እኛም ብንሆን የሚሰማን እንደዚሁ ነው። ይሖዋን ስለምንወደው እሱን መተው ፈጽሞ የማናስበው ነገር ነው።

ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ነፃ ምርጫ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ እናውቃለን። ሽማግሌዎች ምክር አልፎ ተርፎም ተግሣጽ የመስጠት ሥልጣን ቢኖራቸውም የሌሎችን ሕይወት ለመቆጣጠር ወይም በእምነታቸው ላይ ለመሠልጠን አይሞክሩም። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ጸንታችሁ የቆማችሁት በራሳችሁ እምነት ስለሆነ እኛ ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር አብረን የምንሠራ ነን እንጂ በእምነታችሁ ላይ የምናዝ አይደለንም።”—2 ቆሮ. 1:24

አንድን ነገር ተገድደን ሳይሆን በራሳችን ፍላጎት ተነሳስተን ማድረጋችን ደስታ እንደሚያስገኝልን የታወቀ ነው። ይሖዋ በፍቅር ተነሳስተን ጥሩ ነገር እንድናደርግ ይፈልጋል። እንዲህ ማድረጋችን አስፈላጊ መሆኑን ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት ከጻፈው ከሚከተለው ሐሳብ መረዳት ይቻላል፦ “ሌሎችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ እንዲሁም እኮራ ዘንድ ሰውነቴን አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም የማተርፈው ነገር የለም።”—1 ቆሮ. 13:3

ይሖዋ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለእሱ ባላቸው ልባዊ ፍቅር ተነሳስተው ሲያወድሱት ምን ያህል እንደሚደሰት አስቡት!

ይሖዋም ሁሉንም አገልጋዮቹን አጥብቆ ይወዳቸዋል፤ እናንት ወጣቶች እና ልጆች፣ ዓለምንና በውስጥ ያሉትን የሚያባብሉ ነገሮች ችላ በማለት ለእሱ ያላችሁን ፍቅር በማሳየታችሁ ይሖዋ እናንተንም ከልቡ ይወዳችኋል። እኛም በጣም እንደምንወዳችሁ ልናረጋግጥላችሁ እንፈልጋለን።—ሉቃስ 12:42, 43

እናንት ወንድሞችና እህቶች እንዲሁም ወጣቶች ባለፈው ዓመት ለይሖዋ ባላችሁ ፍቅር ተነሳስታችሁ ምሥራቹን በማወጁ ሥራ 1,748,697,447 ሰዓት አሳልፋችኋል። በዓለም ዙሪያ 7,782,346 የሚያህሉ አስፋፊዎች በፍቅር በመገፋፋት በአገልግሎቱ ላይ ተካፍለዋል። ባለፈው ዓመት በርካታ ወጣቶችን ጨምሮ 268,777 የሚያህሉ ሰዎች ራሳቸውን ለይሖዋ መወሰናቸውን በውኃ ጥምቀት ማሳየታቸው አስደስቶናል። ይህ ማለት በየሳምንቱ በአማካይ 5,168 የሚያህሉ ሰዎች ተጠምቀዋል ማለት ነው። በዚህም ልባችን በጣም ተነክቷል!

በእነዚህ በመጨረሻ ቀኖች ውስጥ የአምላክ ሕዝቦች በርካታ ችግሮችን ለመጋፈጥ ተገድደዋል፤ የተለያዩ ተፈታታኝ ሁኔታዎች የሚያጋጥሟቸው፣ ስደት የሚደርስባቸው እንዲሁም በበሽታ የሚሠቃዩ አሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከእርጅና ጋር ተያይዘው ከሚመጡ ችግሮች ጋር ይታገላሉ። ይሁን እንጂ ፈጽሞ ‘አናፈገፍግም’ ወይም ደግሞ “ተስፋ አንቆርጥም።” ሁላችሁንም በጣም እንወዳችኋለን!—ዕብ. 10:39፤ 2 ቆሮ. 4:16

ወንድሞቻችሁ

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ