የርዕስ ማውጫ ሚያዝያ 8 የሚጀምር ሳምንት
ሚያዝያ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 4 ከአን. 1-10 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 10-12 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሉቃስ 12:1-21 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የተለያዩ ዘሮች የተለያየ መልክ የኖራቸው ለምንድን ነው?—rs ገጽ 302 አን. 1 እስከ ገጽ 303 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ይሖዋን እንደ አባታችን አድርገን የምንመለከተው ለምንድን ነው?—ማቴ. 6:9 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ የብርታት ምንጭ ልትሆኑ ትችላላችሁ። (ሮም 1:11, 12) የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። በጉባኤያችሁ ምን ያህል የዘወትር አቅኚዎች እንዳሉ ተናገር። እነሱን ልናበረታታ የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ጥቀስ፤ ለምሳሌ አድናቆታችንን መግለጽ፣ አብሮ ማገልገል፣ የትራንስፖርት ወጪያቸውን መደገፍና ምግብ መጋበዝ ሊሆን ይችላል። አቅኚዎቹ፣ ሌሎች ያበረታቷቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። በጉባኤ ውስጥ የዘወትር አቅኚዎች ከሌሉ ረዳት አቅኚዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ውይይቱን መምራት ትችላለህ።
10 ደቂቃ፦ የመጨረሻዎቹን ቀኖች አስመልክቶ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ መስጠት። በማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 241 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 243 አንቀጽ 1 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ከቀረቡት ሐሳቦች አንዱን በመጠቀም አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “ነቢያትን አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው—ዮናስ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 13 እና ጸሎት