የጥናት እትም ሚያዝያ 15 የሚጀምር ሳምንት
ሚያዝያ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 4 ከአን. 11-18 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሉቃስ 13-17 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሉቃስ 16:16-31 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ፍጽምና የጎደለን መሆናችን በአምላክ ዘንድ ምንም ዓይነት ዋጋ እንዳይኖረን ያደርጋል?—መዝ. 103:8, 9, 14፤ ገላ. 6:9 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የሰው ልጆች በሙሉ የአምላክ ልጆች ናቸው?—rs ገጽ 303 አን. 2 እስከ ገጽ 304 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች—ክፍል 2። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 112 አንቀጽ 3 እስከ ገጽ 113 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አቅኚ ለመሆን ሲሉ ፕሮግራማቸውን ማስተካከል የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ለአንድ ወይም ለሁለት አቅኚዎች ቃለ ምልልስ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ በሥራ ቦታህ ትመሠክራለህ? በውይይት የሚቀርብ፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ (1) የይሖዋ ምሥክር መሆንህን ለሥራ ባልደረቦችህ ማሳወቅህ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? (2) የይሖዋ ምሥክር መሆንህን ማሳወቅ የምትችለው እንዴት ነው? (3) በሥራ ቦታህ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሉህ አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? (4) ከተቻለ መጽሐፍ ቅዱስና አንዳንድ ጽሑፎችን በሥራ ቦታህ ማስቀመጥህ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው? (5) ሥራ ላይ እያለህ ረጅም ምሥክርነት መስጠት የሌለብህ ለምንድን ነው? (6) በሥራ ቦታ በመመሥከር ረገድ ምን ግሩም ተሞክሮ አግኝተሃል?
መዝሙር 45 እና ጸሎት