የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/13 ገጽ 5
  • ውጤት የሚያስገኝ ዘመቻ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውጤት የሚያስገኝ ዘመቻ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቀጥተኛ ግብዣ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ሰዎች በክልል ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የምንጋብዝበት ዘመቻ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ልዩ ግብዣ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • “ክርስቶስን ተከተሉ!” የተባለውን የአውራጃ ስብሰባ በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ የሚደረግ ጥረት በዚህ ዓመትም አስፋፊዎች ልዩ የመጋበዣ ወረቀት ያሰራጫሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 4/13 ገጽ 5

ውጤት የሚያስገኝ ዘመቻ

ጉባኤዎች የአውራጃ ስብሰባቸው ከሚጀመርበት ከሦስት ሳምንት በፊት በክልላቸው የሚገኙ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በስብሰባው ላይ ለመጋበዝ ዘንድሮም በዘመቻ ይካፈላሉ። ይህ ዓመታዊ ዘመቻ የሚደረግበት በቂ ምክንያት አለ። ግብዣውን ተቀብለው ወደ ስብሰባው የሚመጡ ሰዎች በሚሰጡት ቅዱስ ጽሑፋዊ ንግግሮች፣ የሥራ ክፍሎቹ በሚገባ የተደራጁና በዚያም የሚያገለግሉት ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ ሠራተኞች በመሆናቸው እንዲሁም በምናሳየው ጥሩ ምግባርና አንድነት ብዙውን ጊዜ ይማረካሉ። (መዝ. 110:3፤ 133:1፤ ኢሳ. 65:13, 14) ይሁን እንጂ በተለይ ክልላችን የአውራጃ ስብሰባው ከሚካሄድበት ሩቅ በመሆኑ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች በስብሰባው ላይ ለመካፈል ረጅም መንገድ መጓዝ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ዘመቻው ውጤት ይኖረዋል?

የ2011 አውራጃ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ አንድ ቅርንጫፍ ቢሮ፣ መጋበዣ ወረቀቱን በሯ ላይ ካገኘች አንዲት ሴት ደብዳቤ ደርሶት ነበር። ይህች ሴት የይሖዋ ምሥክሮች በሯን ሲያንኳኩ ብዙ ጊዜ ትደበቅ ነበር። እንዲህ በማለት ጽፋለች፦ “ጥሩ ቤት፣ ግሩም ባሕርይ ያለው ባል ስላለኝ ደስታ ሊያስገኙልኝ የሚችሉ ነገሮች በሙሉ እንዳሉኝ ይሰማኝ ነበር። የሚያሳዝነው ግን እነዚህ ነገሮች እያሉኝም ደስታ አልነበረኝም፤ ሕይወቴም እውነተኛ ዓላማ አልነበረውም። በመሆኑም ቅዳሜ ዕለት በሚደረገው ፕሮግራም ላይ ለመገኘት 320 ኪሎ ሜትር የሚሆን መንገድ ነድቼ ለመሄድ ወሰንኩ።” ይህች ሴት በስብሰባው በጣም ስለተደሰተች ለባሏ ስልክ ደውላ በእሁዱ ስብሰባ ላይም ለመገኘት ስትል እዚያ አካባቢ እንደምታድር ነገረችው። እንዲህ ብላለች፦ “ንግግሮቹን በሙሉ ያዳመጥኩ ሲሆን ከበርካታ የይሖዋ ምሥክሮች ጋርም ተዋወቅኩ፤ እንዲሁም ይህ ሁኔታ በዚሁ ብቻ መቅረት እንደሌለበት ወሰንኩ።” ወደ ቤቷ ከተመለሰች በኋላ ጥናት የጀመረች ሲሆን ከአራት ወራት በኋላ ያልተጠመቀ አስፋፊ ሆነች። “የመጋበዣ ወረቀቱን ቤቴ በር ላይ በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ሕይወቴ እውነተኛ ዓላማ አለው!” ብላለች።

የመጋበዣ ወረቀቱ ከሚደርሳቸው ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በስብሰባው ላይ ሊገኙ ይችላሉ። በመሆኑም አስፈላጊ በሆነው በዚህ ዘመቻ ላይ በቅንዓት ተካፈሉ። የቀሯችሁን የመጋበዣ ወረቀቶች ስብሰባው ወደሚደረግበት ከተማ ይዛችሁ በመምጣት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር ተጠቀሙበት።

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

መጋበዣ ወረቀቱን ማሰራጨት የምንችለው እንዴት ነው?

ክልላችንን መሸፈን እንድንችል መግቢያችንን አጭር ማድረግ ያስፈልገናል። እንዲህ ማለት እንችላለን፦ “ጤና ይስጥልኝ። ይህን የመጋበዣ ወረቀት በዓለም ዙሪያ እያሰራጨን ነው። ይህ የእርስዎ ቅጂ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በመጋበዣ ወረቀቱ ላይ ያገኛሉ።” ስትናገሩ ግለት ይኑራችሁ። በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በዘመቻው ስትካፈሉ ሁኔታው የሚያመች ከሆነ መጽሔቶችንም አብራችሁ ማበርከት ይኖርባችኋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ