የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/13 ገጽ 3-4
  • መስማትና መማር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መስማትና መማር
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በመንፈሳዊ ድግስ ላይ ለመገኘት ተዘጋጅተሃል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ‘በማዳመጥ ተጨማሪ ትምህርት ቅሰሙ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • በመንፈሳዊ የምንመገብበትና የምንደሰትበት ዝግጅት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ‘ሕዝቡን ሰብስብ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 4/13 ገጽ 3-4

መስማትና መማር

1. በአውራጃ ስብሰባ ላይ መስማትና መማር እንድንችል ልዩ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል የምንለው ለምንድን ነው?

1 በቅርቡ የ2013 የአውራጃ ስብሰባ ይጀምራል። በዓለም ዙሪያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ የሚያስገባ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ብዙ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ታዲያ በሦስቱም ቀን፣ ስብሰባው ላይ ለመገኘት ዝግጅት አድርገሃል? በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ትኩረትን ሊሰርቁ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ፕሮግራሙን በጥሞና ለመከታተል ልዩ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ከጉባኤ ስብሰባ የበለጠ ጊዜ ስለሚወስድ ለረጅም ጊዜ ትኩረታችንን መሰብሰብ ይኖርብናል። በተጨማሪም በስብሰባው ላይ ለመገኘት የምናደርገው ጉዞና ሌሎች ነገሮች የድካም ስሜት ሊፈጥሩብን ይችላሉ። ታዲያ ንቁ በመሆን መስማትና መማር እንድንችል ምን ሊረዳን ይችላል?—ዘዳ. 31:12

2. ልባችንን በስብሰባው ላይ ለሚቀርቡት ትምህርቶች ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

2 የአውራጃ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት፦ www.pr2711.com/am የተባለው ሕጋዊ ድረ ገጻችን የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራሙን ይዞ ይወጣል፤ ፕሮግራሙ ከያዛቸው ነገሮች መካከል የሁሉም ንግግሮች ርዕሶች እንዲሁም ለእያንዳንዱ ንግግር የተሰጠ አንድ ወይም ሁለት ቁልፍ ጥቅሶች ይገኙበታል። ኢንተርኔት የመጠቀም አጋጣሚው ካለን እነዚህን መረጃዎች አስቀድመን መመልከታችን ልባችንን ለትምህርቱ ለማዘጋጀት ይረዳናል። (ዕዝራ 7:10 የ1954 ትርጉም) ቤተሰባችሁ ስብሰባውን በጉጉት እንዲጠባበቅ ለማድረግ በቤተሰብ አምልኳችሁ ወቅት በፕሮግራሙ ላይ ውይይት ለማድረግ የሚያስችል ጊዜ መመደብ ትችላላችሁ?

3. በጥሞና ለማዳመጥ ምን ሊረዳን ይችላል?

3 በስብሰባው ወቅት፦ ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ በተቻለ መጠን ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት ይህን ማድረጋችሁ ተገቢ ነው። ስብሰባው እየተካሄደ ሳለ ሊደወልላችሁ ወይም መልእክት ሊላክላችሁ ይችላል፤ በዚህ ወቅት ትኩረታችሁ እንዳይሰረቅ ወይም እናንተ ራሳችሁ መልእክት ለመላክ እንዳትፈተኑ የሞባይል ስልካችሁን አጥፉ። ስልካችሁን ማብራታችሁ የግድ አስፈላጊ ከሆነ ሲደወል የሌሎችን ትኩረት እንዳይሰርቅ ስልካችሁ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ይኖርባችኋል። በፕሮግራሙ ላይ እንደ ታብሌት ያሉ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ የሌሎችን ትኩረት እንዳትሰርቁ ተጠንቀቁ። ስብሰባው እየተካሄደ እያለ መመገብ ወይም መጠጣት ተገቢ አይደለም። (መክ. 3:1) ዓይናችሁን በተናጋሪው ላይ አድርጉ። ጥቅስ ሲነበብ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አውጥታችሁ ተከታተሉ። እንዲሁም አጭር ማስታወሻ ያዙ።

4. ወላጆች፣ ልጆቻቸው እንዲሰሙና እንዲማሩ መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው?

4 ልጆቻችንም ጭምር እንዲሰሙና እንዲማሩ እንፈልጋለን። ምሳሌ 29:15 “መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል” ይላል። በመሆኑም ቤተሰቦች አንድ ላይ መቀመጣቸው ጠቃሚ ነው፤ ይህ ደግሞ ወላጆች ልጆቻቸው ከማውራት፣ መልእክት ከመለዋወጥ ወይም ወዲያ ወዲህ ከማለት ይልቅ ስብሰባውን ትኩረት ሰጥተው እየተከታተሉ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላቸዋል። ልጆቹ ገና ሕፃናት በመሆናቸው የሚነገረውን ሁሉ መረዳት ቢቸግራቸውም እንኳ ንቁ ሆነው መከታተልና አርፈው መቀመጥ እንዲለምዱ መሠልጠን ይችላሉ።

5. በስብሰባው ላይ ያገኘናቸውን ትምህርቶች መከለስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?

5 የዕለቱ ስብሰባ ካበቃ በኋላ፦ አታምሹ። በቂ እረፍት እንድታገኙ በጊዜ ተኙ። የሰማችሁትን ነገር መከለሳችሁ ትምህርቱን ቶሎ እንዳትረሱት ይረዳችኋል። በመሆኑም በቤተሰብ አንድ ላይ ሆናችሁ በእያንዳንዱ ዕለት ምሽት ላይ ለጥቂት ደቂቃዎች በፕሮግራሙ ላይ ውይይት ማድረጋችሁ ጠቃሚ ነው። ከጓደኞቻችሁ ጋር ወደ ምግብ ቤት የምትሄዱ ከሆነ በጣም የነኳችሁን አንድ ወይም ሁለት ነጥቦች ለሌላው ለማካፈል እንድትችሉ ለምን ማስታወሻችሁን ይዛችሁ አትሄዱም? ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ የተማራችኋቸውን ነገሮች በቤተሰብ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁ ላይ የተወሰነ ጊዜ መድባችሁ መወያየት ትችሉ ይሆናል። በተጨማሪም አዲስ የወጡ ጽሑፎች ካሉ በየሳምንቱ የተወሰነ ክፍል ለማንበብ ጊዜ መዋጀት ትችላላችሁ።

6. በስብሰባው ላይ መገኘት ብቻ በቂ ነው? አብራራ።

6 ሰዎች በአንድ ድግስ ላይ ሲገኙ የቀረበውን ምግብ ካልተመገቡና ከሰውነታቸው ጋር ካልተዋሃደ ግብዣው መዘጋጀቱ ምንም ትርጉም አይኖረውም። በአውራጃ ስብሰባ ላይ የሚቀርብልንን መንፈሳዊ ግብዣም በተመለከተ ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። በእያንዳንዱ ዕለት በመገኘት፣ በትኩረት በማዳመጥና የተማርነውን ተግባራዊ በማድረግ ከስብሰባው ሙሉ ጥቅም ለማግኘት ጥረት እናድርግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ