ግንቦት 27 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 6 ከአን. 10-18 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዮሐንስ 12-16 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዮሐንስ 12:20-36 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ መሥዋዕት ዋጋ ተጠቃሚዎች እነማን ነበሩ? ዓላማውስ ምን ነበር?—rs ገጽ 308 አን. 1-2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ይሖዋ “ሰላም የሚሰጠው አምላክ” ተብሎ መጠራቱ ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?—ሮም 15:33 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በንግግር የሚቀርብ። በቅርብ ጊዜ የደረሰንን መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ በመጠቀም በሰኔ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ የተከልነውን ዘር ውኃ ማጠጣት። (1 ቆሮ. 3:6-9) በውይይት የሚቀርብ፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ (1) ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ የሚያስደስታችሁ ለምንድን ነው? (2) አንዳንዶች ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ ተፈታታኝ እንዲሆንባቸው የሚያደርጉት ነገሮች ምንድን ናቸው? (3) እነዚህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መወጣት የሚቻለው እንዴት ነው? (4) ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ ከከበደን እርዳታ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? (5) ፍላጎት ያሳያችሁን ሰው መዝግባችሁ ለመያዝ እንዲሁም የተወያያችሁበትን ርዕሰ ጉዳይ፣ ያበረከታችሁለትን ጽሑፍና ሌሎች መረጃዎችን በማስታወሻችሁ ላይ ለማስፈር ምን ዓይነት ዘዴ ትጠቀማላችሁ? (6) ለተመላልሶ መጠየቅ ዝግጅት የምታደርጉት እንዴት ነው? (7) ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ በየሳምንቱ የተወሰነ ጊዜ መመደባችሁ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው?
10 ደቂቃ፦ “ቪዲዮዎችን ለማስተማር ተጠቀሙባቸው።” በውይይት የሚቀርብ። የይሖዋ ምሥክር ከመሆናቸው በፊት ቪዲዮዎቻችንን በመመልከታቸው እንዴት እንደተጠቀሙ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 10 እና ጸሎት