የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ከጥር ወር ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት በተካሄደው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ላይ እንዲካፈሉ የተጋበዙት በአገራችን ያሉ አስፋፊዎች ብቻ ነበሩ። የጥር ወር ሪፖርት የደረሰን ሲሆን በዚህ ወር 133 ወንድሞችና እህቶች ወደ 72 አካባቢዎች ሄደው እንዲያገለግሉ ተመድበዋል። የየካቲትና የመጋቢት ሪፖርት ሲደርሰን ደግሞ በዘመቻው የተካፈሉት ወንድሞችና እህቶች ቁጥር ከፍተኛ እንደሚሆን እንተማመናለን። በመሆኑም በርካታ በግ መሰል ሰዎች እንደሚገኙና መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚያጠኑ ተስፋ እናደርጋለን።