ሰኔ 10 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 37 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 7 ከአን. 1-8 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ የሐዋርያት ሥራ 1-4 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ 1:15 እስከ 2:4 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በቤዛው ምክንያት ወደፊት ምን ዓይነት በረከቶች ይመጣሉ?—rs ገጽ 309 አን. 2 እስከ ገጽ 310 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ በዛሬው ጊዜ የሚገኙ የበርካታ ሰዎች አስተሳሰብ በመርዛማ አየር የተመሰለው ለምንድን ነው?—ኤፌ. 2:1, 2 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ የምናነጋግራቸውን ሰዎች በደንብ ማየት ያለው ጥቅም። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 124 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 125 አንቀጽ 4 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ ሲመሠክር የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ፤ በመጀመሪያው ሠርቶ ማሳያ ላይ አስፋፊው የሚያነጋግረውን ሰው በደንብ አይመለከተውም። ሠርቶ ማሳያውን በድጋሚ በሚያቀርብበት ወቅት ግን የሚያነጋግረውን ሰው በደንብ ይመለከተዋል።
10 ደቂቃ፦ ምን አከናውነናል? የጉባኤው ጸሐፊ በውይይት የሚያቀርበው። በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ምን እንደተከናወነ ጥቀስ፤ እንዲሁም በዚያ ወቅት ላደረገው እንቅስቃሴ ጉባኤውን አመስግን። የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ ሲያሰራጩ ወይም ረዳት አቅኚ ሆነው ሲያገለግሉ ያገኟቸውን የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ “ማስተካከያ ለማድረግ ፈቃደኞች ናችሁ?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 14 እና ጸሎት