ሐምሌ 8 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 8 ከአን. 10-17 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ የሐዋርያት ሥራ 15-17 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ 16:16-34 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አንድ ክርስቲያን ስደት ሲደርስበት ደስተኛ ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው?— ማቴ. 5:11, 12 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር ለመሆን “ይነጠቃሉ” ብሎ ሲናገር እያብራራ የነበረው ርዕሰ ጉዳይ ምን ነበር?—rs ገጽ 311 አን. 3 እስከ ገጽ 312 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ምሥራቹን የምንሰብክባቸው መንገዶች—ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ወደ ይሖዋ ድርጅት መምራት። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 99 ከአንቀጽ 1-3 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አድማጮች ጥናቶቻቸውን ወደ ድርጅቱ ለመምራት የይሖዋ ፈቃድ የተባለውን ብሮሹር የተጠቀሙት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ ይሖዋን ፈትኑት፤ ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የተትረፈረፈ በረከት ታገኛላችሁ (ሚል. 3:10) ለሁለት ወይም ለሦስት የዘወትር አቅኚዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። ከአቅኚነት አገልግሎታቸው በጣም የሚወዱት ምንድን ነው? አቅኚ መሆናቸው መንፈሳዊነታቸውን ለማጠናከር የረዳቸው እንዴት ነው? ያገኙት አስደሳች ተሞክሮ ካለ እንዲናገሩ ጠይቃቸው። አስፋፊዎች መስከረም ላይ አቅኚ መሆን ይችሉ እንደሆነ እንዲያስቡበት በማበረታታት ደምድም።
10 ደቂቃ፦ “ነቢያትን አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው—ኢዩኤል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 54 እና ጸሎት