ሐምሌ 15 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 48 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 8 ከአን. 18-22 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ የሐዋርያት ሥራ 18-21 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ የሐዋርያት ሥራ 20:17-38 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ክርስቶስ ዓለም እየተመለከተው በደመና መጥቶ ታማኝ ክርስቲያኖችን ወደ ሰማይ ይወስዳቸዋል?—rs ገጽ 312 አን. 2 እስከ ገጽ 313 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ “በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር” የምንችለው እንዴት ነው?—ሮም 8:6 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ የጥናቶቻችሁን ልብ ለመንካት ጥረት አድርጉ። (ሉቃስ 24:32) በውይይት የሚቀርብ፤ እነዚህን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ (1) ጥናት ስንመራ የሚከተሉትን ጉዳዮች ጎላ አድርገን መግለጻችን ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው? (ሀ) የይሖዋን ፍቅርና ጥበብ፣ (ለ) የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን መከተል ያለውን ጥቅም፣ (ሐ) ውሳኔ ከማድረጋችን በፊት ምንጊዜም የይሖዋን አመራር የመጠየቅን አስፈላጊነት። (2) ጥናታችሁን የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቃችሁ ልቡ መነካት አለመነካቱን ለመገንዘብ የሚረዳችሁ እንዴት ነው? (ሀ) ይህ ሐሳብ ምክንያታዊ ይመስልሃል? (ለ) ይህ ሐሳብ አምላክ አፍቃሪ ከመሆኑ ጋር ይስማማል ብለህ ታስባለህ? (ሐ) ይህን ምክር ተግባራዊ ማድረግህ ምን ጥቅም የሚያስገኝልህ ይመስልሃል?
20 ደቂቃ፦ “ወጣት ወንድሞች፣ የኃላፊነት ቦታ ላይ ለመድረስ እየተጣጣራችሁ ነው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በወጣትነቱ የኃላፊነት ቦታ ላይ ለደረሰ አንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርግለት። የጉባኤ አገልጋይ ከመሆኑ በፊት ምን ሥራ ወይም ሥልጠና ተሰጥቶት ነበር? ሌሎች የጉባኤው አባላት መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርግ የረዱት እንዴት ነው? የኃላፊነት ቦታ ላይ ለመድረስ መጣጣሩ ምን በረከቶችን አስገኝቶለታል?
መዝሙር 26 እና ጸሎት