የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በጥር ወር ያደረግነው እንቅስቃሴ ጎላ ያሉ ገጽታዎች፦ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር 9,532፣ ከፍተኛ የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር 1,920። በተጨማሪም 26,024 የሚያህሉ ብሮሹሮች ተበርክተዋል፤ ይህም ከጥር 2005 ወዲህ ብሮሹር በማበርከት ረገድ የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር ነው። እባካችሁ ለእነዚህ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ አድርጎላቸው፤ እንዲሁም ምሥራች የተባለውን ብሮሹር በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስጀምሯቸው።