ነሐሴ 12 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 10 ከአን. 1-10 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሮም 5-8 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ሮም 6:21 እስከ 7:12 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አንዳንድ ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር እንዲሆኑ ወደ ሰማይ የሚወሰዱት ለምንድን ነው?—rs ገጽ 315 አን. 5-8 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ በቁሳዊ ረገድ አስተማማኝ የሆነ ነገር ለመያዝ መጣር ለጥፋት ሊዳርግ ይችላል የምንለው ለምንድን ነው?—ማቴ. 6:33፤ 1 ጢሞ. 6:10 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ “የአምላክ ቃል ለማስተማር ይጠቅማል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የወረዳ ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን የሚታወቅ ከሆነ ተናገር።
10 ደቂቃ፦ አስተዋጽኦ መጠቀም በአገልግሎታችን ውጤታማ ለመሆን የሚረዳን እንዴት ነው። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 166 አንቀጽ 5 እስከ ገጽ 167 አንቀጽ 4 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ አገልግሎት ከመውጣቱ በፊት ጥቂት ደቂቃዎች ወስዶ በወሩ የሚበረከተውን ጽሑፍ ለሰዎች ለማበርከት የሚጠቀምበትን መግቢያ በአእምሮው ሲያቀናብር የሚያሳይ መነባንብ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። የሐዋርያት ሥራ 8:26-31 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
መዝሙር 29 እና ጸሎት