መስከረም 16 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 21 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 11 ከአን. 15-21 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ቆሮንቶስ 1-7 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ቆሮንቶስ 1:15 እስከ 2:11 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በሪኢንካርኔሽንና መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው ተስፋ መካከል ምን ያህል ልዩነት አለ?—rs ገጽ 319 አን. 3-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አንድ ሰው የይሖዋን ስም መጠጊያው ለማድረግ ምን ማድረግ አለበት?—ሶፎ. 3:12 NW (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ወጣቶች—በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል?—ክፍል 2። ወጣቶች በተባለው ትራክት ከአንቀጽ 10 እስከ መጨረሻው ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በወጣትነት ዕድሜው በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለተካፈለ አንድ አስፋፊ ቃለ ምልልስ አድርግ። የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ እንዲገባ ያነሳሳው ምንድን ነው? ምን በረከቶችን አግኝቷል?
10 ደቂቃ፦ ብቻችሁን ስታገለግሉ። በውይይት የሚቀርብ፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ (1) የአገልግሎት ጓደኛ ሳይኖረን በምንሰብክበት ጊዜ ደስታችንን ለመጠበቅ የሚረዳን ምንድን ነው? (2) ብቻችንን ተመላልሶ መጠየቅ በምናደርግበት ጊዜ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገናል? (3) እኛ አገልግሎት በምንወጣባቸው ቀናት የመስክ ስምሪት ስብሰባ ባይኖር በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወንድሞች አብረውን እንዲወጡ ማበረታታት የምንችለው እንዴት ነው? (4) ሁኔታዎች አመቺ በሚሆኑባቸው ጊዜያት አስበንበት ብቻችንን ማገልገላችን ምን ጥቅሞች አሉት?
10 ደቂቃ፦ “በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ብሮሹሩ የተዘጋጀበትን መንገድና ገጽታዎቹን በአጭሩ ከልስ።—የመጋቢት 2013 የመንግሥት አገልግሎታችንን ገጽ 5 ተመልከት።
መዝሙር 16 እና ጸሎት