መስከረም 23 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 12 ከአን. 1-7 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ቆሮንቶስ 8-13 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ቆሮንቶስ 10:1-18 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ፦ ‘እኔ በሪኢንካርኔሽን አምናለሁ’—rs ገጽ 320 አን. 1-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ 1 ቆሮንቶስ 10:13ን መረዳት የሚኖርብን እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ “እናንተ የእኔን ጽሑፍ ከወሰዳችሁ እኔም የእናንተን እወስዳለሁ።” በውይይት የሚቀርብ። እንዲህ ያለ ሐሳብ ሲቀርብላቸው ውጤታማ በሆነ መንገድ መልስ የሰጡት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ያደረገውን እንቅስቃሴ ከልስ። ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ጉባኤውን አመስግን። በሚመጣው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚችላቸውን አንድ ወይም ሁለት የአገልግሎት ዘርፎች ጥቀስ፤ ከዚያም በዚህ ረገድ ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦችን ተናገር።
15 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። የሐዋርያት ሥራ 16:19-40 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
መዝሙር 44 እና ጸሎት