ታኅሣሥ 9 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 25 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 15 ከአን. 17-20 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዮሐንስ 1 እስከ ይሁዳ (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ዮሐንስ 5:1-21 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ክርስቶስ መታወስ ያለበት እንዴት ነው?—ሉቃስ 1:32, 33፤ ዮሐ. 17:3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ትክክለኛው ሃይማኖት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እውነተኛ እምነት እንዳለው በተግባር ያሳያል—rs ገጽ 328 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ የ2014 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት። በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ከ2014 የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ ላይ ለጉባኤው የሚያስፈልጉ አንዳንድ ነጥቦችን ጥቀስ። ለሳምንቱ የተመደበው ንባብ የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፎች የያዘ በሚሆንበት ጊዜ ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርበው ወንድም ከአሁን በኋላ ክፍሉን የሚያቀርበው “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው ከሚሉት ብሮሹሮች ላይ እንዳልሆነ ተናገር። በተጨማሪም የተማሪ ክፍል ቁጥር 2 እና ክፍል ቁጥር 3 የሚቀርቡት ከማመራመር መጽሐፍ ላይ በሚሆንበት ጊዜ የሚቆጠሩት ገባ ብለው የሚጀመሩ አንቀጾች ብቻ ናቸው። ሁሉም አስፋፊዎች ክፍል ሲሰጣቸው ተገኝተው በማቅረብ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጎላ ያሉ ነጥቦች ላይ ሐሳብ በመስጠት እንዲሁም ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ላይ በየሳምንቱ የሚሰጡትን ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትጉዎች እንዲሆኑ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “ውጤታማ መግቢያዎችን ማዘጋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። የመጀመሪያው ሠርቶ ማሳያ ላይ ውጤታማ ያልሆነ መግቢያ ሲጠቀሙ ይታያል፤ በሁለተኛው ላይ ግን ውጤታማ የሆነ መግቢያ ይጠቀማሉ።
መዝሙር 23 እና ጸሎት