ታኅሣሥ 16 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 16 ከአን. 1-6 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 1-6 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ራእይ 3:14 እስከ 4:8 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ እውነተኛው ሃይማኖት ለይስሙላ የሚደረግ የአምልኮ ሥርዓት ሳይሆን የሕይወት መንገድ ነው—rs ገጽ 328 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ‘አርዓያ የሆነላቸው’ በየትኞቹ መንገዶች ነው?—ዮሐ. 13:15 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ምን አከናውነናል? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። የመንግሥት ዜና ቁ. 38 በተሰራጨበት ወቅት ከጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል ውስጥ ምን ያህሉ እንደተሸፈነ ለጉባኤው ተናገር። በዘመቻው መካፈላቸው ምን ጥቅም እንዳስገኘላቸው እንዲሁም ያገኟቸውን አስደሳች ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ ወጣቶች ይሖዋን ያወድሱ። (መዝ. 148:12, 13) ምሳሌ ለሚሆኑ ሁለት ወይም ሦስት ወጣቶች ቃለ መጠየቅ አድርግ። በትምህርት ቤት ውስጥ በእምነታቸው ምክንያት ምን ፈተናዎች አጋጥመዋቸዋል? እነዚህን ፈተናዎች መቋቋም እንዲችሉ ወላጆቻቸውና ሌሎች ሰዎች የረዷቸው እንዴት ነው? ስለ ክርስቲያናዊ አቋማቸው በግልጽ እንዲናገሩ ድፍረት የሰጣቸው ምንድን ነው? ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ “‘ስለ አምላክ መንግሥት የተሟላ ምሥክርነት መስጠት።’” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 28 እና ጸሎት