ታኅሣሥ 30 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 13 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 16 ከአን. 15-20 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 15-22 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ “‘በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ’ እርዷቸው።” በንግግር የሚቀርብ። በንግግሩ መጨረሻ ላይ፣ በጥር ወር የመጀመሪያው ቅዳሜ ጥናት ለማስጀመር መጽሔቶችን መጠቀም የሚቻለው እንዴት እንደሆነ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም በዚህ ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታቸው።
10 ደቂቃ፦ ልጃችሁ አስፋፊ እንዲሆን እርዱት። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 82 አንቀጽ 1-2 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ያልተጠመቀ አስፋፊ የሆነ ልጅ ላለው ምሳሌ የሚሆን አንድ ወላጅ ቃለ መጠይቅ አድርግ። ልጁ እድገት እንዲያደርግና አስፋፊ ለመሆን የሚያስፈልገውን ብቃት እንዲያሟላ የረዳው እንዴት ነው?
10 ደቂቃ፦ ፈጽሞ ብቻችንን አይደለምን። (2 ነገ. 6:16) በ2013 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 48 አንቀጽ 1-3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
መዝሙር 20 እና ጸሎት