የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በአገልግሎት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አሥር ወራት ማለትም እስከ ሰኔ ማብቂያ ድረስ 487 የሚያህሉ ሰዎች በአውራጃ፣ በወረዳና በልዩ ስብሰባዎች ላይ ተጠምቀዋል። በእነዚሁ ወራት ከሠላሳ በላይ ልዩ ስብሰባዎች በአሥራ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ ተደርገዋል። በአሁኑ ጊዜ ተጓዥ የበላይ ተመልካቾቻችን 240 የሚያህሉ ቦታዎችን ይጎበኛሉ። ከእነዚህ ቦታዎች መካከል አሥራ ሦስቱ በ2013 የአገልግሎት ዓመት የተቋቋሙ አዳዲስ ቡድኖች ወይም ጉባኤዎች ናቸው፤ ይህም አንድ አዲስ ወረዳ ለማቋቋም ከሚያስፈልገው የጉባኤዎች ቁጥር ግማሽ ያህሉ ማለት ነው። እነዚህ ሁሉ አዳዲስ ሰዎች ከይሖዋ ጎን ሲቆሙ ማየት መቻላችን ያስደስተናል!