የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ብዙ ሰዎች አምላክን በተመለከተ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች አምላክ ሚስጥራዊ ኃይል እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ በሰማይ እንዳለ አፍቃሪ አባት አድርገው ይመለከቱታል። እርስዎስ አምላክ ምን ዓይነት ነው ብለው ያስባሉ?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የጥር 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በመጨረሻው ገጽ ላይ ያለውን ዓምድ አሳየው። ከዚያም በመጀመሪያው ጥያቄ ሥር ባለው ሐሳብ እና በአንቀጹ ላይ ካሉት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“የመጣነው፣ የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት ስለሚያሳድርብን ስሜት አጠር ያለ ውይይት ለማድረግ ነው፤ ደግሞም እንዲህ ያለ ነገር የማያጋጥመው ሰው የለም። የቅርብ ጓደኛን ወይም ዘመድን በሞት ማጣት በጣም ከባድ ነገር ነው ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጽናንቷቸዋል። [ኢሳይያስ 25:8ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ሞት የማይኖርበት ጊዜ እንደሚመጣና የምንወዳቸው ሰዎች ትንሣኤ እንደሚያገኙ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎችን ያብራራል።”
ንቁ! ጥር
“በዛሬው ጊዜ የቤተሰብ ሕይወት በርካታ ተፈታታኝ ነገሮች አጋጥመውታል ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፣ የቤተሰብ አባላት አንድነታቸውን ለማጠናከር ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይናገራል። [ምሳሌ 24:3ን አንብብ።] ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ የጥበብ ምንጭ እንደሆነ ተገንዝበዋል። ይህ መጽሔት ለቤተሰብ ሕይወት ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦች በነፃ ስለሚገኙበት አንድ ድረ ገጽ ያብራራል፤ ድረ ገጹ ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው።”