ጥር 13 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥር 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 17 ከአን. 10-15 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 6-10 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 9:18 እስከ 10:7 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ፦ ‘በኢየሱስ እስካመንህ ድረስ የየትኛውም ቤተ ክርስቲያን አባል ብትሆን ለውጥ የለውም’—rs ገጽ 331 አን. 3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አሮን—ሰብዓዊ ድክመቶች ቢኖሩበትም ታማኝ ሆኖ ቀጥሏል—w10 5/15 ገጽ 21 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ መደጋገም በአገልግሎት ላይ ያለው ጥቅም። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 206 እስከ ገጽ 207 አንቀጽ 5 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ከቀረቡት ነጥቦች ቢያንስ አንዱን በመጠቀም አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ በተገቢው ሁኔታ የሚያገለግሉ ወንዶች። (1 ጢሞ. 3:13) ለሁለት የጉባኤ አገልጋዮች ቃለ ምልልስ አድርግ። በጉባኤ ውስጥ ያሉባቸው ኃላፊነቶች ምንድን ናቸው? እነዚህ ኃላፊነቶቻቸውን ለመወጣት ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? ለዚህ ኃላፊነት ለመብቃት እንዲጣጣሩ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? ጉባኤውን ማገልገልም ሆነ የጉባኤ ሽማግሌዎችን መርዳት የሚያስደስታቸው ለምንድን ነው?
10 ደቂቃ፦ “ነቢያትን አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው—ሚክያስ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 35 እና ጸሎት