የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 24, 2014 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. ሰይጣን፣ ሔዋን በምን ነገር ላይ እንድታተኩር አደረጋት? ሔዋን ከተከለከለው ፍሬ መብላቷስ ምን ያሳያል? (ዘፍ. 3:6) [ጥር 6, w11 5/15 ገጽ 16-17 አን. 5]
2. አቤል ጠንካራ እምነት ያዳበረው እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዲህ ያለ እምነት ማዳበሩ ምን ውጤት አስገኘ? (ዘፍ. 4:4, 5፤ ዕብ. 11:4) [ጥር 6, w13 1/1 ገጽ 12 አን. 3፤ ገጽ 14 አን. 4-5]
3. ወላጆች፣ ልጆቻቸው “በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ” ዓለማውያንን እንዳያደንቁ ጥበቃ ሊያደርጉላቸው የሚችሉት እንዴት ነው? (ዘፍ. 6:4) [ጥር 13, w13 4/1 ገጽ 13 አን. 2]
4. በዘፍጥረት 19:14-17 እና 26 ላይ ከሚገኘው፣ ስለ ሎጥና ስለ ሚስቱ ከሚገልጸው ዘገባ ምን እንማራለን? [ጥር 27, w03 1/1 ገጽ 16-17 አን. 20]
5. አብርሃም በትንሣኤ ተስፋና ዘሩ በይስሐቅ በኩል እንደሚመጣ ይሖዋ በሰጠው ተስፋ ላይ እምነት እንዳለው ያሳየው እንዴት ነው? (ዘፍ. 22:1-18) [የካ. 3, w09 2/1 ገጽ 18 አን. 4]
6. በዘፍጥረት 25:23 ላይ ተመዝግቦ ከሚገኘው “ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” ከሚለው ትንቢት ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? [የካ. 10, w03 10/15 ገጽ 29 አን. 2]
7. ያዕቆብ ስለ መሰላል የተመለከተው ሕልም ትርጉሙ ምንድን ነው? (ዘፍ. 28:12, 13) [የካ. 10, w04 1/15 ገጽ 28 አን. 6]
8. ላባ የተሰረቀውን ተራፊም ለማስመለስ ብርቱ ጥረት ያደረገው ለምንድን ነው? (ዘፍ. 31:30-35 የ1954 ትርጉም) [የካ. 17, g 11/07 ገጽ 18 አን. 1፤ it-2-E ገጽ 186 አን. 2]
9. በዘፍጥረት 32:29 ላይ ተመዝግቦ ከሚገኘው መልአኩ ለያዕቆብ ከሰጠው መልስ ምን እንማራለን? [የካ. 24, w13 8/1 ገጽ 10]
10. ዲና ያጋጠማት ነገር እንዳይደርስብን መከላከል የምንችልበት አንዱ መንገድ ምንድን ነው? (ዘፍጥረት 34:1, 2) [የካ. 24, w01 8/1 ገጽ 20]