መጋቢት 3 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
jl ትምህርት 5-7 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 36-39 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1: ዘፍጥረት 37:1-17 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2: ከሞት የተነሱ ሰዎች ቀደም ሲል በሠሯቸው ነገሮች ምክንያት የማይፈረድባቸው ለምንድን ነው?—rs ገጽ 337 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3: አቢግያ—ይሖዋን የሚያስከብሩ ባሕርያትን ማሳየት—w09 7/1 ገጽ 18-21 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በመጋቢት ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ከመክፈቻው ሐሳብ ጀምሮ እስከ መደምደሚያው ድረስ ተራ በተራ ተወያዩበት። በመጋቢት ወር የመጨረሻዎቹ ሁለት ቅዳሜና እሁዶች ላይ ከመጋበዣ ወረቀቱ ጋር መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ በመጋበዝ ክፍልህን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በማስታወሻ ላይ መመዝገብ።” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው፤ እንዲሁም ያገኙትን ግሩም ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 1 እና ጸሎት