ማስታወቂያዎች
◼ የካቲት፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! ወይም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። (አምላክን ስማ የሚለውን ብሮሹር፣ ማንበብ የማይችል ወይም የማንበብ ችሎታው ውስን የሆነ ሰውን ለማወያየት ልንጠቀምበት እንችላለን።) መጋቢት እና ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ግንቦት፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ወይም ትራክቶች።
◼ በ2014 በሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “አፍቃሪ የሆነ አምላክ ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?” የሚል ነው።
◼ በጠረጴዛ ወይም በጋሪ ተጠቅማችሁ የአደባባይ ምሥክርነት በምትሰጡበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስን ሰዎች እንዲያዩት መደርደር የለባችሁም። ከዚህ ይልቅ ለሚጠይቋችሁ ወይም ለእውነት ልባዊ ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች አውጥታችሁ መስጠት ትችላላችሁ።
◼ መጋዘናችን ውስጥ አዲስ የገቡ፦ ተሻሽሎ የወጣው አዲስ ዓለም ትርጉም (እንግሊዝኛ)፤ ለውይይት የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች (ወላይትኛ)