ማስታወቂያዎች
◼ ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ግንቦት እና ሰኔ፦ ትራክቶች። ሐምሌ፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! ወይም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። (አምላክን ስማ የሚለውን ብሮሹር፣ ማንበብ የማይችል ወይም የማንበብ ችሎታው ውስን የሆነ ሰውን ለማወያየት መጠቀም እንችላለን።)
◼ በ2014 የአገልግሎት ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “በዓለም ላይ ከሚመጣው መከራ መዳን” የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።
◼ ጉባኤዎች የአውራጃ ስብሰባቸውን ወይም ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ለማድረግ አንድ ሳምንት ሲቀራቸው በሚያደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ላይ ማስተካከያ በማድረግ በዚህ የመንግሥት አገልግሎት ላይ የቀረቡትን ምክሮችና ማሳሰቢያዎች እንዲሁም መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ላይ ስንገኝ ልንወስዳቸው ስለሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች በሚናገረው ለሁሉም ጉባኤዎች በተላከው የነሐሴ 3, 2013 ደብዳቤ ላይ የወጡትን ሐሳቦች መከለስ ይኖርባቸዋል። ስብሰባው ከተደረገ ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት በሚለው ክፍል ላይ አስፋፊዎች ከአውራጃ ስብሰባው ለአገልግሎት ጠቃሚ ሆነው ያገኟቸውን ሐሳቦች መከለስ ይቻላል።