ግንቦት 5 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 1 ከአን. 10-15 እና በገጽ 12 ላይ የሚገኝ ሠንጠረዥ (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 23-26 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፀአት 25:1-22 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አዳም የሰንበትን ሕግ እንደጠበቀ የሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ የለም—rs ገጽ 345 አን. 5 እስከ ገጽ 346 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አብርሃም—ማን ነበር?—w12 1/1 ገጽ 3-4 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በግንቦት ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሁለት የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ከመክፈቻው ሐሳብ ጀምሮ እስከ መደምደሚያው ድረስ ተራ በተራ ተወያዩበት። ሁሉም ከመጽሔቶቻችን ጋር በደንብ እንዲተዋወቁና በቅንዓት እንዲያሰራጩ አጠር ያለ ማበረታቻ በመስጠት ክፍልህን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥሩ የአገልግሎት ጓደኛ ሁኑ” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። እንዲሁም ያገኙትን ግሩም ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 45 እና ጸሎት