የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
“የአምላክ ቃል እውነት ነው!” በሚል ጭብጥ ያደረግናቸው 25 የአውራጃ ስብሰባዎች በድምሩ 17,011 የደረሰ ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥርና 258 የተጠማቂዎች ቁጥር በማስመዝገብ ተጠናቅቀዋል። የመጋበዣ ወረቀቶችን ለማሰራጨት ያደረግነው ዘመቻ ይህ ከፍተኛ ቁጥር እንዲገኝ አስተዋጽኦ አድርጓል። በስብሰባው ላይ ከተገኙት ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች መካከል የአንድ ወንድም ጎረቤት ይገኝበታል፤ ይህ ሰው የመጋበዣ ወረቀቱ ከደረሰው በኋላ 200 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዞ በስብሰባው ላይ ተገኘ። በሌላ በኩል ደግሞ 612 አቅኚዎች፣ በአቅኚዎች የአገልግሎት ትምህርት ቤት የተካፈሉ ሲሆን በመንፈሳዊነትና በአገልግሎት ላይ ያተኮረ ጥሩ ሥልጠና አግኝተዋል።