ግንቦት 12 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 1 ከአን. 16-21 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 27-29 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፀአት 29:19-30 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኢየሱስ የሙሴን ሕግ “የሥነ ሥርዓት” ሕግጋትና “የሥነ ምግባር” ሕግጋት በማለት አልከፋፈለውም—rs ገጽ 346 አን. 3 እስከ ገጽ 347 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አብርሃም—የእምነት ሰው—w12 1/1 5-6 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ። (ኢሳ. 2:2) ለሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ፤ አንደኛው በእውነት ውስጥ በርካታ ዓመታት የቆየ፣ ሌላኛው ደግሞ ወደ እውነት የመጣው በአንጻራዊ ሁኔታ በቅርብ ሊሆኑ ይገባል። እውነትን እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ምንድን ነው? ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎችን መወጣት አስፈልጓቸዋል? ለመጀመሪያ ጊዜ በጉባኤ ስብሰባ ላይ ሲገኙ ትኩረታቸውን የሳበው ምንድን ነው? ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት በወጡበት ጊዜ ስለነበረው ሁኔታ ምን የሚያስታውሱት ነገር አለ? መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ ሌሎች የጉባኤው አባላት የረዷቸው እንዴት ነው?
15 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—መግቢያ ማዘጋጀት።” በውይይት የሚቀርብ። ሁለት ክፍሎች ያሉት አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጀመሪያው ክፍል አስፋፊው በደንብ ያልታሰበበት መግቢያ ሲጠቀም የሚያሳይ ነው፤ በሁለተኛው ክፍል ላይ ግን ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት መግቢያ ይጠቀማል። ጊዜ በፈቀደ መጠን ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 215-219 ላይ ተስማሚ የሆኑ ነጥቦችን ጥቀስ።
መዝሙር 20 እና ጸሎት