ግንቦት 19 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 2 ከአን. 1-7 እና በገጽ 13 ላይ የሚገኘው የመግቢያ ሐሳብ (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 30-33 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፀአት 32:1-14 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አሥርቱ ትእዛዛት ከሙሴ ሕግ ጋር ተሽረዋል—rs ገጽ 347 አን. 2-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አብርሃም—ደፋር ሰው—w12 1/1 ገጽ 6-7 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ የምሥራቹ አገልጋዮች የሆንነው ለምንድን ነው? የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 77 እስከ ገጽ 78 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በግለት የሚቀርብ ንግግር። አድማጮች አገልግሎት የሚያስደስታቸው ለምን እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ በእረፍት ጊዜያችሁ ረዳት አቅኚ መሆን ትችላላችሁ? በውይይት የሚቀርብ። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 112 አንቀጽ 4 ላይ የሚገኙትን ረዳት አቅኚ ለመሆን የሚያስፈልጉ ብቃቶች በአጭሩ ከልስ። ከዚያም ከሥራ ፈቃድ ወስደው ወይም ትምህርት ቤት ሲዘጋ ረዳት አቅኚ ሆነው ያገለገሉ አስፋፊዎች ያገኙትን በረከት እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁሉም እረፍት በሚወጡበት ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆነው እንዲያገለግሉ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ “ሰዓት አክባሪ የመሆንን ልማድ አዳብሩ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 4 ላይ ስትወያዩ አድማጮች ሰዓት አክባሪ እንዲሆኑ የረዳቸው ምን እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 44 እና ጸሎት