ግንቦት 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 2 ከአን. 8-15 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 34-37 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፀአት 34:1-16 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አሥርቱ ትእዛዛት መሻራቸው የሥነ ምግባር ገደብ መነሳቱን አያመለክትም የምንለው ለምንድን ነው?—rs ገጽ 348 አን. 1-2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አብርሃም—ትሑት ሰው—w12 1/1 ገጽ 9-10 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በማስጀመር ረገድ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በሰኔ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። እንዲሁም ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ ስደትን በጽናት መቋቋም ጥሩ ምሥክርነት ለመስጠት ያስችላል። (ሉቃስ 21:12, 13) በ2013 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) በገጽ 124 አንቀጽ 1 እና በገጽ 128 አንቀጽ 1-2 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። አንድ ሽማግሌ በውይይት የሚያቀርበው። በልጅነታቸው ከወላጆቻቸው ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን በመማራቸው የተጠቀሙ አስፋፊዎች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 41 እና ጸሎት