ማስታወቂያዎች
◼ ግንቦት እና ሰኔ፦ ትራክቶች። ሐምሌ፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! ወይም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። (አምላክን ስማ የሚለውን ብሮሹር፣ ማንበብ የማይችል ወይም የማንበብ ችሎታው ውስን የሆነ ሰውን ለማወያየት መጠቀም እንችላለን።) ነሐሴ፦ ትራክቶች ወይም የሚከተሉት ብሮሹሮች፦ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የምትወዱት ሰው ሲሞት ወይም የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ። በተጨማሪም ከ2011 በፊት የታተሙ በእጃችሁ ያሉ በመስክ ለማሰራጨት ተብለው የተዘጋጁ ሌሎች ብሮሹሮችን ማበርከት ትችላላችሁ።
◼ መጋዘናችን ውስጥ አዲስ የገቡ፦ የ2013 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዝ (አማርኛ)፣ ምሥራች (ሶማልኛ)፣ የይሖዋ ፈቃድ (የኮንጎ ስዋሂሊ)።