ሰኔ 2 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 55 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 2 ከአን. 16-23 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 38-40 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፀአት 40:20-38 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ሰንበት ለክርስቲያኖች ምን ትርጉም አለው?—rs ገጽ 348፤ w11 7/15 ገጽ 27 አን. 16-17 ላይ ማስተካከያ ተደርጎበታል (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አብርሃም—አፍቃሪ ሰው—w12 1/1 ገጽ 10-11 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በሰኔ ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሁለት የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ከመክፈቻው ሐሳብ ጀምሮ እስከ መደምደሚያው ድረስ ተራ በተራ ተወያዩበት። ሁሉም ከመጽሔቶቻችን ጋር በደንብ እንዲተዋወቁና በቅንዓት እንዲያሰራጩ አጠር ያለ ማበረታቻ በመስጠት ክፍልህን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—መግቢያ ማዘጋጀት” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። እንዲሁም ያገኙትን ግሩም ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 44 እና ጸሎት