ሰኔ 30 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 4 ከአን. 1-4 እና በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 14-16 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ “ወዲያውኑ ተከታትላችሁ እርዷቸው።” በንግግር የሚቀርብ። ከዚያም በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በሐምሌ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ የግል ጥናት ጠንካራ አገልጋዮች ያደርገናል። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 27-32 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ጥሩ የጥናት ልማድ በማዳበሩ ለሚታወቅ አንድ አስፋፊ ቃለ መጠይቅ አድርግ።
መዝሙር 11 እና ጸሎት