የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 30, 2014 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
መዝናኛ በምንመርጥበት ወቅት በዘፀአት 23:2 ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት ግምት ውስጥ ማስገባታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ዘፍ. 39:7-12) [ግን. 5, w11 7/15 ገጽ 10-12 አን. 3-7]
ካህናቱ መሥዋዕቶችን ለይሖዋ ከማቅረባቸው በፊት እንዲታጠቡ የሚያዝዘው ሕግ ምን ያህል ክብደት የሚሰጠው ነበር? ይህ ሕግ በዛሬው ጊዜ ላሉ የአምላክ አገልጋዮች ጠንካራ ማሳሰቢያ የሚሆናቸውስ እንዴት ነው? (ዘፀ. 30:18-21) [ግን. 19, w96 7/1 ገጽ 9 አን. 9]
አሮን የወርቅ ጥጃ በመሥራቱ ያልተቀጣው ለምንድን ነው? (ዘፀ. 32:1-8, 25-35) [ግን. 19, w04 3/15 ገጽ 27 አን. 4]
ክርስቲያኖች ስለ መጠናናትና ስለ ትዳር ያላቸው አመለካከት እስራኤላውያን ይሖዋን የማያመልኩ ሰዎችን እንዳያገቡ አምላክ ከሰጣቸው ሕግ ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው? (ዘፀ. 34:12-16) [ግን. 26, w89-E 11/1 ገጽ 20-21 አን. 11-13፤ w11 12/15 ገጽ 10 አን. 13-14]
የባስልኤልና የኤልያብ ታሪክ የሚያበረታታን እንዴት ነው? (ዘፀ. 35:30-35) [ግን. 26, w10 9/15 ገጽ 10 አን. 13]
የእስራኤል ሊቀ ካህናት በጥምጥሙ ላይ ‘የተቀደሰ የአክሊል ምልክት’ ማድረጉ ለምን ነገር ማሳሰቢያ ይሆነው ነበር? ይህ ምልክት ራስን ስለ መወሰን ምን ያስተምረናል? (ዘፀ. 39:30 የ1954 ትርጉም) [ሰኔ 2, w01 2/1 ገጽ 14 አን. 2-3]
ሁሉም ክርስቲያኖች፣ አንድ የእምነት ባልንጀራቸው ከባድ ኃጢአት በሚሠራበት ወቅት ምን የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው? (ዘሌ. 5:1) [ሰኔ 9, w97 8/15 ገጽ 27]
የኅብረት መሥዋዕት በጥንት ዘመን ምን አስፈላጊ ቦታ ነበረው? ይህ መሥዋዕት በዛሬው ጊዜ የሚያመለክተው ምንን ነው? (ዘሌ. 7:31-33) [ሰኔ 16, w12 1/15 ገጽ 19 አን. 11-12]
የአሮን ልጆች የናዳብና የአብዩድ ኃጢአት ምንን የሚጨምር ሊሆን ይችላል? እኛስ ከዚህ ዘገባ ምን እንማራለን? (ዘሌ. 10:1, 2, 9) [ሰኔ 23, w04 5/15 ገጽ 22 አን. 6-8]
ልጅ መውለድ አንዲትን ሴት ‘የሚያረክሳት’ ለምንድን ነው? (ዘሌ. 12:2, 5) [ሰኔ 23, w04 5/15 ገጽ 23 አን. 2]