ሐምሌ 7 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 30 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 4 ገጽ 33 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 17-20 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 19:19-32 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች ወይም “ቅዱሳን” ከኃጢአት ነፃ ያልሆኑት ለምንድን ነው?—rs ገጽ 354 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ጥልቁ—መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጥልቁ ምን ይላል?—w12 9/15 ገጽ 7 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሁለት የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ከመክፈቻው ሐሳብ ጀምሮ እስከ መደምደሚያው ድረስ ተራ በተራ ተወያዩበት። ሁሉም ከመጽሔቶቻችን ጋር በደንብ እንዲተዋወቁና በቅንዓት እንዲያሰራጩ አጠር ያለ ማበረታቻ በመስጠት ክፍልህን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን አከናውነናል? የጉባኤው ጸሐፊ በውይይት የሚያቀርበው። በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ምን እንደተከናወነ ጥቀስ፤ እንዲሁም በዚያ ወቅት ላደረገው እንቅስቃሴ ጉባኤውን አመስግን። የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ ሲያሰራጩ ወይም ረዳት አቅኚ ሆነው ሲያገለግሉ ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 42 እና ጸሎት