የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በታኅሣሥ ወር የመንግሥት ዜና ቁ. 38ን ለማሰራጨት ዘመቻ አድርገን ነበር፤ በዚህ ዘመቻ ጥሩ ተሳትፎ በማድረጋችሁ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን! የአስፋፊዎች አማካይ ሰዓት 13.5 የነበረ ሲሆን ይህም ከነሐሴ 2011 ወዲህ የተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር ነው። በአጠቃላይ 292,859 ትራክቶችና ብሮሹሮች የተበረከቱ ሲሆን ይህም ተከታትለን ልንረዳቸው የሚገባ ፍላጎት ያላቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ የሚጠቁም ነው። በተጨማሪም 1,986 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር በመመዝገቡ በጣም ተደስተናል። ይህ ቁጥር በቅርቡ 2,000 እንደሚደርስ ተስፋ እናደርጋለን!