ሐምሌ 14 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 1 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 4 ከአን. 5-12 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 21-24 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 23:1-14 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የሰው ልጆች በሙሉ እንደሚድኑ መጠበቅ ቅዱስ ጽሑፋዊ አይደለም—rs ገጽ 355 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ተቀባይነት ያለው ጊዜ—የአምላክን ሞገስ ለማግኘት አመቺ የሆነውን ጊዜ በጥበብ ተጠቀሙበት—w10 12/15 ገጽ 11-15 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በነሐሴ ወር ለሚካሄደው ልዩ ዘመቻ ተዘጋጁ። በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? የተባለው አዲሱ ትራክት ለሌላቸው አድማጮች ትራክቱ እንዲታደል አድርግ። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። የመጀመሪያው ሠርቶ ማሳያ ትራክቱን ለቤቱ ባለቤት የምናበረክተው እንዴት እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ሁለተኛው ሠርቶ ማሳያ ደግሞ የቤቱ ባለቤት ፍላጎት ካሳየ ወይም መወያየት ከፈለገ ትራክቱን እንዴት ልናበረክትለት እንደምንችል ያሳያል። ሁሉም በዘመቻው የቻሉትን ያህል ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ።
5 ደቂቃ፦ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር ከተባለው ቡክሌት ጥቅም ማግኘት። በውይይት የሚቀርብ። የዕለት ጥቅስ መቼ መቼ እንደሚያነቡና ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር የተባለው ቡክሌት ምን ጥቅም እንዳስገኘላቸው እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
15 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ከሰዎች ጋር ውይይት በመጀመር መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር።” በውይይት የሚቀርብ። አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 16 እና ጸሎት