መስከረም 1 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 46 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 6 ከአን. 17-24 እና በገጽ 48 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 17-21 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 17:1-13 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ዲያብሎስ ስለመኖሩ እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን?—rs ገጽ 360 አን. 1 እስከ ገጽ 361 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የሐዋርያት ሥራ—የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ትክክለኛነት—bsi08-1 ገጽ 14-15 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሁለት የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ከመክፈቻው ሐሳብ ጀምሮ እስከ መደምደሚያው ድረስ ተራ በተራ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ስለ መንግሥቱ በድፍረት መናገር” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። በድፍረት ስለ መንግሥቱ መናገር ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዳሉት ከግል ተሞክሯቸው በመነሳት እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። እነዚህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች የተወጡትስ እንዴት ነው?
10 ደቂቃ፦ የልዩ ዘመቻው ውጤት። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። መንግሥቱን በማስታወቁ ሥራ ወደፊት መግፋታችን ያለውን አስፈላጊነት በተመለከተ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ላይ የወጡትን ዋና ዋና ነጥቦች ከልስ። ጉባኤው ለዚህ ማሳሰቢያ ምላሽ የሰጠው እንዴት ነው? በዚህ ዘመቻ ምን ጎላ ያሉ ክንውኖች ነበሩ?
መዝሙር 45 እና ጸሎት