የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ልዩ የአገልግሎት ዘመቻው በየካቲት ወርም ቀጥሎ ነበር። ከአሥር የተለያዩ አገሮች ከ60 የሚበልጡ ወንድሞችና እህቶች እኛን ለመርዳት በመምጣታቸው በጣም ተደስተናል። ከ500 የሚበልጡ በአገሪቱ የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶችም በዚህ ዘመቻ የተካፈሉ ሲሆን ቢያንስ 169 የአገልግሎት ምድቦች ተሸፍነዋል። ከእነዚህ መካከል በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ምሥራቹ የተሰበከው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ይህም በዚህ ወር 7,765 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ሪፖርት እንዲደረጉ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ ይህ አኃዝ ከሚያዝያ 2013 ወዲህ የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር ነው። ሁላችሁም ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትላችሁ በመርዳት ረገድ ብሎም ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ በንቃት እንድትካፈሉ እናበረታታችኋለን።