መስከረም 8 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 49 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 7 ከአን. 1-8 እና በገጽ 53 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 22-25 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 22:36 እስከ 23:10 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ሰይጣን በሰው ውስጥ ያለ የክፋት ባሕርይ አይደለም—rs ገጽ 361 አን. 2 እስከ ገጽ 362 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አዳም—የተፈጠረው በይሖዋ አምሳል ነው የምንለው ከምን አንጻር ነው?—w11 2/15 ገጽ 9 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ በአገልግሎት ላይ መልካም ምግባር አሳዩ። (2 ቆሮ. 6:3) በውይይት የሚቀርብ፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ (1) በምናገለግልበት ጊዜ መልካም ምግባር ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው? (2) በሚከተሉት ጊዜያት መልካም ምግባር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (ሀ) አብረን ከተመደብናቸው አስፋፊዎች ጋር ወደ አገልግሎት ክልሉ ስንደርስ፣ (ለ) ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ስንሄድ ወይም በገጠር ክልል ውስጥ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላኛው ረጅም ርቀት በምንጓዝበት ወቅት፣ (ሐ) የቤቱ በር ላይ ስንቆም፣ (መ) የአገልግሎት ጓደኛችን ሲመሠክር፣ (ሠ) የቤቱ ባለቤት ሲናገር፣ (ረ) የቤቱ ባለቤት ሥራ ላይ ከሆነ ወይም የአየሩ ጠባይ መጥፎ ሲሆን እንዲሁም (ሰ) የቤቱ ባለቤት ጥሩ ምላሽ በማይሰጥበት ጊዜ።
15 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት መጣል።” በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ ለአገልግሎት ሲዘጋጅ የሚያሳይ መነባንብ እንዲቀርብ አድርግ፤ በዚህ ወቅት አስፋፊው የሚያነጋግረው ሰው መጽሔቶችን ከወሰደ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት የሚወያዩበት ምን ጥያቄ ማንሳት እንደሚችል ያስባል።
መዝሙር 38 እና ጸሎት