መስከረም 22 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 9 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 7 ከአን. 14-18 እና በገጽ 57 እና 58 ላይ የሚገኙ ሣጥኖች (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 30-32 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 32:16-30 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ሰይጣን እንዳመፀ አምላክ ወዲያው ያላጠፋው ለምንድን ነው?—rs ገጽ 362 አን. 3 እስከ ገጽ 363 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አስተዳደር—ከአዳም ዘመን አንስቶ እስከ መጀመሪያው መቶ ዘመን ድረስ የኖሩ ሰብዓዊ አስተዳዳሪዎች—w10 1/15 ገጽ 24-28 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ ብልጽግና የሚያስገኝ የሚስዮናዊነት ሕይወት። (ምሳሌ 10:22) በ2014 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 123 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 127 አንቀጽ 4 እና በገጽ 169 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
15 ደቂቃ፦ “jw.orgን በአገልግሎታችሁ ላይ ተጠቀሙበት።” በውይይት የሚቀርብ። በአንቀጽ 2 ላይ የሚገኘውን አቀራረብ በመጠቀም አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ከዚያም ለአድማጮች የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርብላቸው፦ እንደ ሞባይል ስልክ ባሉ ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻችን ላይ ቪዲዮውን መጫናችን ምን ጥቅሞች አሉት? ለምናነጋግረው ሰው ስለ ቪዲዮው ብዙ ሳንናገር ወይም ቪዲዮውን ለማየት ይፈልግ እንደሆነ ሳንጠይቀው ማጫወት መጀመራችን ብዙውን ጊዜ የተሻለ የሚሆነው ለምንድን ነው? ቪዲዮውን በአገልግሎት ላይ በመጠቀም ረገድ ምን ተሞክሮዎች አግኝታችኋል? አስፋፊዎች በjw.org ላይ ካሉት የተለያዩ ገጽታዎች ጋር በደንብ እንዲተዋወቁ እንዲሁም ድረ ገጹን በአገልግሎታቸው ላይ እንዲጠቀሙበት በማበረታታት ክፍሉን ደምድም።
መዝሙር 25 እና ጸሎት