የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 27, 2014 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
በዘኍልቍ 21:5 ላይ እንደተገለጸው እስራኤላውያን በአምላክና በሙሴ ላይ ያጉረመረሙት ለምንድን ነው? ይህ ዘገባ ለእኛስ ምን የማስጠንቀቂያ ትምህርት ይዟል? [መስ. 1, w99 8/15 ገጽ 26-27]
ይሖዋ በበለዓም ላይ በጣም የተቆጣው ለምንድን ነው? (ዘኍ. 22:20-22) [መስ. 8, w04 8/1 ገጽ 27 አን. 3]
ዘኍልቍ 25:11 ፊንሐስ ስለነበረው ዝንባሌ ምን ይነግረናል? የእሱን ምሳሌ መከተል የምንችለውስ እንዴት ነው? [መስ. 8, w04 8/1 ገጽ 27 አን. 5]
ሙሴ በትሕትና ረገድ ምሳሌ የተወልን በየትኞቹ መንገዶች ነው? (ዘኍ. 27:5, 15-18) [መስ. 15, w13 2/1 ገጽ 5]
የኢያሱና የካሌብ ሕይወት፣ ፍጽምና የጎደላቸው የሰው ልጆች ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም አምላክ በሚፈልገው መንገድ መመላለስ እንደሚችሉ ጠንካራ ማስረጃ የሚሆነው እንዴት ነው? (ዘኍ. 32:12) [መስ. 22, w93 11/15 ገጽ 14 አን. 13]
ነጠላ የሆኑ ክርስቲያኖች ስለ ጋብቻ ባላቸው አመለካከት ረገድ ከሰለጰዓድ ሴት ልጆች ታዛዥነት ምን ይማራሉ? (ዘኍ. 36:10-12) [መስ. 29, w08 2/15 ገጽ 4-5 አን. 10]
እስራኤላውያን ማጉረምረማቸውና አሉታዊ ነገር መናገራቸው ምን መዘዝ አስከትሎባቸዋል? እኛስ ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘዳ. 1:26-28, 34, 35) [ጥቅ. 6, w13 8/15 ገጽ 11 አን. 7]
እስራኤላውያን በተስፋይቱ ምድር ከይሖዋ በረከትና ብልጽግና ለማግኘት የትኛውን ድርብ ኃላፊነት መወጣት ነበረባቸው? (ዘዳ. 4:9) [ጥቅ. 13, w06 6/1 ገጽ 29 አን. 15]
እስራኤላውያን በምድረ በዳ በተጓዙበት ወቅት ልብሳቸው አላረጀም እግራቸውም አላበጠም ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (ዘዳ. 8:3, 4) [ጥቅ. 20, w04 9/15 ገጽ 26 አን. 1]
ከይሖዋ “ጋር ተጣበቁ” የሚለውን ለእስራኤላውያን የተሰጠ ማሳሰቢያ ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? (ዘዳ. 13:4, 6-9) [ጥቅ. 27, w02 10/15 ገጽ 16 አን. 14]