ጥቅምት 27 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 9 ከአን. 8-18 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 11-13 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ “በስብከቱ ሥራችን የጥድፊያ ስሜት እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?” በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ወይም አንድ ትራክት ሲያበረክት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ በጥድፊያ ስሜት ለማገልገል በሚገባ ተዘጋጁ። በነሐሴ 15, 2014 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 14 አንቀጽ 14 እስከ ገጽ 15 አንቀጽ 20 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በጉባኤው ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚያስጨንቁ ጉዳዮች ወይም ጥያቄዎች የትኞቹ እንደሆኑ አድማጮችን ጠይቅ። በአገልግሎታችን ላይ እነዚህን ጉዳዮች ግምት ውስጥ ማስገባት የምንችለው እንዴት ነው? ሁለት አቅኚዎች ወይም አንድ ባልና ሚስት በመጽሔቱ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ተጠቅመው ለጉባኤያቸው ክልል የሚስማማ መግቢያ ሲዘጋጁ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያውን የሚያቀርቡት አስፋፊዎች የትኛውን ጽሑፍ ማበርከት እንዳለባቸው ራሳቸው ሊወስኑ ይችላሉ።
መዝሙር 1 እና ጸሎት